ይህን ቅፅ በመሙላት በሁሉም መመሪያዎችና ህጎች መሰረት ተስማምተዋል ማንኛውም ጥያቄ ካሎት ቅድሚያ እባክዎ ከዚህ በታች ባለው ስልክ እና አድራሻ ያነጋግሩን / By completing this form, you agree to comply with all policies and laws. If you have any questions, please contact us by phone and address below.
መመሪያዎችና ህጎች፡- እባክዎን ይህን ማመልከቻ በቅድሚያ ያንብቡና ይሙሉት በመቀጠል ቪዲዮዎትን አዘጋጅተው በድረ-ገፃችን ላይ በመጫን ወይም በTelegram ወይም በWhatssApp አዲስ አበባ በ09-44-73-22-17 አሜሪካ +1571-340-5829 እንዲሁም በFacebook ይላኩልን፡፡ በአካል መጥቶ ለመመዝገብም ሆነ ቪዲዮ ለማስረከብ ወይም ለበለጠ መረጃ አዲስ አበባ 09-09-60-36-70 ይደውሉ፡ / Policies and Rules: Please read this application first and fill out this form and then record your video and upload it on our web site or via Telegram or WhatssApp in Addis Ababa at 09-44-73-22-17, US + 1571-340-5829 and Facebook. To register and submit a video, please call us on 09-09-60-36-70.
የተወዳዳሪዎች ምዝገባ ህዳር 23 ቀን 2011 ዓ.ም ተጀምሯል፡፡ / Candidates Registration has started on December 2, 2018.
በድምፅ፣ በዳንስ፣ በስፖርት፣ በስነ-ጥበብ (ስዕል)፣ በፈጠራ፣ በትወና፣ በፊልም፣ በድራማ ፣ በኮሜዲ፣ በልዩ ተሰጥዖና በሌሎች በመሳሰሉት ወዘተ ተወዳዳሪ መሆን ይችላሉ፡፡ / You can compete in the vocal, dance, sports, art, drawing, acting, film, drama, comedy, special talent, and so on.
ቪዲዮው ከየካቲት 27 ጀምሮ በአምባሰል ቲዩብ ተጭኖ ለእይታ ይቀርባል፡፡ / The video will be available starting from March 6, 2019 on Ambassel Tube
የት፡- በመላው አለም ማንኛውም ዜጋ በኦንላይን መመዝገብ ይችላል እንዲሁም በኢትዮጵያ ያለ በአካል መጥቶ ለመመዝገብ የፈለገ አዲስ አበባ በ09-0960-36-70 ደውለው ቢሮ በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ፡፡ / Where- Anyone can register online and can register in person by registering in person at Addis Ababa, 09-0960-36-70
ማን፡- ሁሉም የእድሜ ክልል ውስጥ ያለ መመዝገብ ይችላል፡፡ በይበልጥ ታዳጊ፣ ወጣቶች እና ሴቶች ለዚህ ይበረታታሉ፡፡ / Who: Any age group can register Youngsters and women are encouraged.
ለማሸነፍ መስፈርት፡- አንድ ቪዲዮ ብልጫ ላይክ ያለው ቪዲዮ ብቻ አሸናፊ ይሆናል፡፡ በመጨረሻ የመወዳደሪያ ሰዓት ላይ 60,000 ብር ይሸለማል፡፡ / Criteria to win: Only one video with the most “Likes” on Ambassel Tube’s Youtube channel will be selected as winnner and will be awarded 60,000 birr.
እያንዳንዱ ቪዲዮ የመወዳደሪያ ቁጥር ይሰጠዋል እንዲሁም የተወዳዳሪ ስም ይመዘገባል፡፡ / Each video will be labeled with a competitor number and competitor's name.
ለአምባሰል ቲዩብ ታለንት ውድድር የሚልኩት የተለያየ ታለንት ያለው ቪዲዮ እስከ ነሐሴ 23 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡ ቪዲዮው ደቂቃው ባይበዛ ይመረጣል፡፡ / The deadline of the video submission is until It may be that the video that has been different to the 2013 Thunderbolt Tweets contest may have been until August 29, 2019. It’s preferable if the video is few minutes long.
የመጨረሻ የውድድሩ የመዝጊያ ቀን ነሐሴ 27/2011 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡ በዚች ሰዓት ላይ አንድ ቪዲዮ ከሁሉ ለመወዳደር ከቀረቡት ብልጫ ላይክ ያለው አሸናፊ ይሆናል፡፡ ይህንን በጥብቅ ይከታተሉ!!! / The closing date for the closing date is September 2, 2019 at 3:00 pm. At this moment, the video with the most ”Likes” will be the winner of the contest. Track this closely!!!
የላኩት ቪዲዮ ተገምግሞ መስፈርቱን ካሟላ ቪዲዮዎን በአምባሰል ቲዩብ ላይ ይለቀቃል፡፡ እባክዎ ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችለውን ተሰጥዖ ብቻ ይላኩ፡፡ ነገር ግን ሀይማኖትን የሚነቅፍ፣ ፖለቲካ ነክ የሆነ፣ አስነዋሪ ድርጊት ከሆነ፣ እርቃን መታየት እና ግለሰብን የሚነቅፍ ማንኛውም ቪዲዮ ውድቅ ይሆናል፡፡ / If the video you submitted has been reviewed and approved, your video will be published on Ambassel Tube. Please send only genuine talent, any video containing nudity, politics, religion, and discrimination will be disqualified
ተወዳዳሪዎች በቡድን ወይም በግለሰብ ስም ተመዝግበው ታለንታቸውን በቪዲዮ አቅርበው ሊወዳደሩ ይችላሉ፡፡ / Contestants can be in groups or individual
ተወዳዳሪዎች አስር ያህል ተመሳሳይ ወይም የተለያዩ ታለንቶች ያላቸውን ቪዲዮዎችን ለመወዳደሪያ መላክ ይችላሉ፡፡ ግን የሚያሸንፈው ከጠቅላላ ተወዳዳሪ አንዱ ብቻ ይሆናል፡፡ / Contestants can submit multiple videos but each video will have its own like counts and the one with greater “Like” will be selected.
አንድ ቪዲዮ ብቻ ለአሸናፊነት እና ለሽልማት ይመረጣል፡፡ / Only one video will be selected as winner.
ተወዳዳሪዎች በአምባሰል ቲዩብ ላይ የተጫነውን ቪዲዮዎቻቸውን ሼር በማድረግ እና እንዲደረግላቸው ሌላውን በማስተባበር እንዲሁም በማህበራዊ ገፆች በመረጡት መንገድ የማስተዋወቅ ሀላፊነት አለባቸው፡፡ / Every contestant has the responsibility of promoting his/her video on social media or anyway they prefer.
ማንኛውም ታለንት ተወዳዳሪው ለሚልከው ቪዲዮ ለሚመጣው ማንኛውም ጥያቄ ሙሉ ኃላፊነት ይወስዳል እና ስለ ቪዲዮው ለሚነሳ ማንኛውም ጥያቄ ወይም ጉዳይ ተጠያቂነቱ የታለንት ተወዳዳሪው ብቻ ይሆናል፡፡ አቅራቢው ድርጅት በሚቀርቡት ታለንት ቪዲዮዎች ላይ ኃላፊነት አይወስድም ተጠያቂም አይሆንም፡፡ / Contestants are responsible for the content they provide and they will be responsible for any question or issue that arises regarding their video.
ይህ ውድድር በኢትዮጵያ ህግ በአማርኛው በተፃፈው መሰረት ይመራል፡፡ / This competition is governed by the Ethiopian law (Amharic version).
ተወዳዳሪው ከውድድሩ በፊት ወይም በኃላ የላከውን ቪዲዮ ከቻናሉ ላይ እንዲወርድ የመጠየቅ መብት የለውም፡፡ ነገር ግን የተጫነው ቪዲዮ ጥያቄ የሚያስነሳ እና ችግር ያለበት ከሆነ ድርጅቱ አምባሰል ቲዩብ ኮንቴስት ያወርደዋል፡፡ ማንኛውም ለሚወርዱ ቪዲዮዎች ድርጅቱ ተጠያቂ አይደለም፡፡ / Contestant will not have right to request to remove the video before or after the contest after submitted. But if the uploaded video raises a problem and the problem Ambassel Tube has the right to remove the video and will not be responsible for the removed videos.
ተወዳዳሪዎች ተመልካቶቻቸውን ወይም ደጋፊዎቻቸውን ሰብስክራይብ እንዲያደርጉ እና ላይክ እንዲያደርጉ ሊያሳውቁ ወይም ሊገፋፉ ጥረት እንዲያደርጉ ይመከራል፡፡ / It is strongly recommended that contestants inform or encourage their audience to “Like” their videos.
የውድድሩ ጥቅሞች ሀ/ በዓለም አቀፍ ደረጃ ራስን ማስተዋወቅ እና ዝና ማግኘት ለ/ ተሰጥዖን ማሳየት እና ካሸነፉ ተሸላሚ መሆን / Benefits of the contest – a) introducing oneself internationally and gaining fame. b) Showing talent to the rest of the world and getting award if greatest YouTube like, and exposing self to more opportunities.